አሁኑኑ ትምህርትዎን ይጀምሩ!

 

ተመዝግበዋል?

መፅሐፉን ገዝተው ከሆነ ሲመዘገቡ ሁሉንም የድምፅ ቅጂዎች በነፃ ያገኛሉ።
መፅሐፉን ገና ካልገዙ ሲመዘገቡ ሁለት ምዕራፎችን እና ጥቂት የድምፅ ቅጂዎችን በነፃ ያገኛሉ።

ለመመዝገብ እዚህ ክሊክ ያድርጉ

በጥቂት ሰዓታት ውስጥ በቻይንኛ ይነጋገሩ!

ይህ ኮርስ በትንሽ ጊዜ ውስጥ ቻይንኛ እንዲማሩ ያስችልዎታል።!

ቻይንኛን በአማርኛ ቋንቋ መማር ይችላሉ!

ይህ መፅሐፍ ለአማርኛ ተናጋሪዎች ታስቦ የተፃፈ ስለሆነ በቀላሉ ቻይንኛን ለመማር ያስችልዎታል። መፅሐፉን አንብቦ ለመረዳት ምንም የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ አያስፈልግዎትም። ቻይንኛን በቀላሉ አሁኑኑ ይማሩ።

በድምፅ ቅጂ የታገዘ ትምህርት

ቋንቋን መፅሐፍ በማንበብ ብቻ መማር አይቻልም። ለዚህም ነው ይህ መፅሐፍ ከድምፅ ቅጂ ጋር ሆኖ የሚመጣው። የድምፅ ቅጂው እያንዳንዱ ቃል እንዴት እንደሚነበብ ያሳይዎታል። የሰሙትን ደጋግመው ሲናገሩ ደግሞ ልምድ ያካብታሉ።

ቻይናውያን እንዴት እንደሚነጋገሩ ይሰማሉ

ይህ መፅሐፍ የልምምድ ምዕራፎችም አሉት። በእነዚህ መዕራፎች ውስጥ ቻይናውያን ሲነጋገሩ ይሰማሉ። ስለዚህ ከቻይናውያን ጋራ በሚነጋገሩበት ጊዜ በቀላሉ ይገባዎታል!

ከተማሪዎቻችን

የTVET ኮሌጅ መምህር ነኝ። ይህ መፅሐፍ ለHSK 2 ፈተናዬ እንድዘጋጅ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጎልኛል። HSKየቻይንኛ ቋንቋ ችሎታን የሚለካ አለም አቀፋዊ ፈተና ነው። ቻይናም ሀገር በሄድኩበትም ጊዜ መፅሐፉ እብሮኝነበር። ከቻይኖች ጋራ እንድግባባ እረድቶኛል። ለዚህም በጣም አመሰግናለሁ።

– ቤቴልሔም ላቀው

በንግዱ ዘርፍ ነው የተሰማራሁት። መፅሐፉን በማንበብ ላይ እገኛለው። በጣም ወድጄዋለው። በቀላሉ እንዲገባተደርጎ የተፃፈ ነው። ፀሐፊዋም እጅግ በጣም ጥሩ አስተማሪ ናት።

– ፀጋ መዝገቡ

www.chineseforethiopia.com የተሰኘው ዌብሳይት ላይ ከተመዘገብኩ በኋላ የሚላክልኝ መረጃ በተለይምስለቻይና ባህል ላይ የሚያተኩሩት መረጃዎች በጣም አስደስተውኛል። ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ጠቃሚ ናቸው።

– ስማቸው አለን ሙሴ

ስሜ ፍቅርተ መላኩ ይባላል። መሀንዲስ ነኝ። መፅሀፉን ገዝቼ እያነበብኩ ነው ነገር ግን የምሰራበት አካባቢ ቻይንኛ የሚችል ሰውም ሆነ የቻይና ተወላጅ ባለመኖሩ ያነበብኩት ነገር ተመልሶ ይጠፋብኛል። ምናልባት እንደፈተና አይነት ነገር ትምህርቱ ቢኖረውና የተሻለ ውጤት ያመጣል ብዬ አስባለሁ። በተረፈ ግን ጥሩ ጅምር ነው። በዚሁ ቀጥሉ!

– ፍቅርተ መላኩ

ዉሐን በተሰኘችው የቻይና ከተማ ነው የምኖረው። የሁዋጆንግ አግሪካልቸራል ዩኒቨርሲቲ የPhD ተማሪ ስሆን የዩኒቨርሲቲ ሌክቸረር ሆኜም አገልግያለሁ። ይህ መፅሐፍ ለብዙ ጊዜ የጠበኩት ሲሆን በጉጉት ነበር ያነበብኩት። ለኢትዮጵያውያን ቻይንኛ በቀላሉ እንዲገባ ተብሎ ነው የተዘጋጀው። የአስተማሪ እርዳታ ሳያስፈልግ በዚህ መፅሐፍ መማር ይቻላል። ሌሎች በእንግሊዘኛ የተፃፉ የቻይንኛ መማሪያ መፅሐፎች በካራክተሮች የተሞሉ ቢሆኑም ስለቋንቋው ግን ምንም ማብራሪያ አይሰጡም። ፀሐፊዋ ሊና ግን ብዙ ሰዓት ወስዳ ለአንባቢዎች እንዲገባ አድርጋ ነው የፃፈችው። የመፅሐፉም ጥንካሬ ይኸው ነው።

– ሀይማኖት አትንኩት

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሌክቸረር ነኝ። መፅሐፉን እስከ አዲስ አበባ ከተማ ድረስ በመጓዝ ነው የገዛሁት። ምን ያህል መፅሐፉ እንደረዳኝ ለመግለፅ ያዳግተኛል። አጠቃቀሙ በጣም በጣም ቀላል ነው። ወደፊት ቻይንኛ እንደምለምድ አሳምኖኛል። በደንብ እያጠናሁ እገኛለሁ። ለሰጣችሁን እድል በጣም አመሰግናለሁ።

– ሰይፉ ከበደ ወ/ጊዮርጊስ

ዌብሳይቱ ላይ ከተመዘገብኩ በኋላ የሚላኩልኝ ኢሜሎች እና መረጃዎች ማራኪ ናቸው። አመሰግናልሁ። እግዜአብሄር ይባርካችሁ።

– ዮሐንስ ወ/ጊዮርጊስ

ኢትዮጵያ ውስጥ ረዳት ፕሮፌሰር ስሆን እዚህ ቻይና ደግሞ የPhD ፌሎ ነኝ። ይህ መፅሐፍ ለቻይንኛ ቋንቋ ጀማሪዎች በጣም ጥሩ ነው። የድምፅ ቅጂዎቹ ደግሞ የቻይንኛ ቶኖችን ለመማር በጣም  ጠቃሚ ናቸው። ይህ መፅሐፍ ለማንኛውም ወደ ቻይና ለመጓስ ሀሳብ ላለው ወይም ከቻይናዎች ጋራ ለመስራት ፍላጎት ላለው ኢትዮጵያዊ ጠቃሚ ነው ብዬ አስባለሁ።

– ሄኖክ አምባቸው ሀይሌ

ይህ መፅሐፍ በጣም ጠቃሚ ሆኖ ነው ያገኘሁት። በአሁኑ ጊዜ መፅሐፉን እያነበብኩ እና የድምፅ ቅጂውን እያዳመጥኩ እገኛለሁ። በጣም አስደስቶኛል።

– ዮሐንስ ገ/መድህን

የኮሚኒኬሽን ኢንጂኒር ስሆን በኢቲዮ ቴሌኮም ነው የምሰራው። የHSK የጀማሪዎችን ፈተና ተፈትኛለሁ። HSK የቻይንኛ ቋንቋ ችሎታን የሚለካ አለም አቀፋዊ ፈተና ነው። ይህ መፅሐፍ በጣም ረድቶኛል። ወደፊት በኢንተርኔት ላይ የተመሰረተ ኮርስ ቢዘጋጅ ደስ ይለኛል። የHSK ፈተና እንድንፈተንም ቢረዳን ጥሩ ነው። መጪው ጊዜ ጥሩ የቋንቋ ልምድ የምናካብትበት ጊዜ እንዲሆን እመኛለሁ።

  – ዮሐንስ አደመ

ቻይንኛ እንድንማር ይህ መፅሐፍ የሚያደርግልን ድጋፍ በጣም ደስ የሚል ነው። የጥናት ዘዴዎቹ ደግሞ በጣም ጥሩ ናቸው። ቻይንኛን እንዲህ በቀላሉ እማራለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር።

– ልዑልሰገድ ተስፋይ

ይህ መፅሐፍ እና የድምፅ ቅጂዎቹ በጣም አስደስተውኛል። ቃላቶች ያንሱኛል። በጣም አመሰግናለሁ።

– መስፍን ከማል

የስራ መደቤ ምህንድስና ነው። ቻይንኛን ለማስተማር ለምታደርገው ልዩ ጥረት ፀሐፊዋን ለማመስገን እወዳለሁ።

– አሰግድ መንግስቴ

በአንድ የጨርቃጨርቅ ኩባንያ ውስጥ ከፍተኛ የአካውንቲንግ ባለሞያ ነኝ። ኩባንያችን ውስጥ ከተለያዩ ሀገሮች የመጡ ሰዎች አሉ። ለምሳሌ ከህንድ፥ ስሪላንካ፥ኬንያ እና ቻይና። ኢትዮጵያውያንም በብዛት ይገኛሉ። እስካሁን ድረስ መፅሐፉን አልከዛሁም። ነገርግን ሁለት በነፃ የሚሰጡትን ምዕራፎች አንብቤያለሁ። በጣም ጥሩ ናቸው። ዌብሳይቱ (www.chineseforethiopia.com) ላይም ከተመዘገብኩ በኋላ የሚላኩልኝ ስለቻይና ባህል የሚተነትኑ ኢሜሎችም በጣም አስደስተውኛል።

– አሪያም ደባስ

መጽሐፉን ገመግዛቴ አንድ ወር በኋላ ወደ ቻይና ስኮላርሺፕ አግኝቼ ሄጄ እዛው ነኝ ያለሁት። እዳጋጣሚ ሆኖ መጽሐፏ በእጄ በመኖሯ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ብዙ ኢትዮጵያውያን እየተጠቀሙባት ነው። እንዲያውም የቻይንኛ ኮርስ  እየወሰድን ነን እና መጽሐፏ በሚገባ እየረዳችኝ ነው። እዚህ ከምንማርበት መጽሐፍ የተሻለ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ያለመምህር የምታስተምር ምርጥ መጽሀፍ ነች።

– መላክ ታዬ

የስራ ዘርፌ ቱሪዝም ነው። ጀርመንኛም መናገር እችላለሁ። ይህ ብዙ በሮችን ከፍቶልኛል። ለዛም ቢዬ ነው ቻይንኛ ለመማር የወሰንኩት። የዳሉን የመጀመሪያ ሁለት ምዕራፎች በዌብሳይቱ ላይ በመመዝገብ አንብቤያለሁ። በጣም ወድጃቸዋለሁ። አስተማመሩ እጅግ በጣም ጥሩ ነው።

– ሞላ ምህረቱ

በትንሽ ጊዜ ውስጥ ቻይንኛን አቀላጥፈው መናገር ይችላሉ!

ቻይንኛን በቀላሉ ተምረው ህይወትዎን ይለውጡ። ይህ መፅሐፍ እና አብሮት የሚመጣው የድምፅ ቅጂ በቀላሉ እና በሚገባ መልኩ ቋንቋውን ያስተምርዎታል።

ሰላምታ

 

እራስን ማስተዋወቅ

 

እንግዳን ሲቀበሉ

 

ምግብ ማዘዝ

 

ግብይት

 

መንገድ ላይ

 

ሆስፒታል ሲሄዱ

 

እነዚህን ጨምሮ ሌሎች ብዙ ምዕራፎች ተካተዋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

በአለማችን የመጀመሪያው ቻይንኛን በአማርኛ ቋንቋ የሚያስተምር መፅሐፍ!

ቻይንኛን በአማርኛ ቋንቋ መማር ይችላሉ!

ይህ መፅሐፍ ለአማርኛ ተናጋሪዎች ታስቦ የተፃፈ ስለሆነ በቀላሉ ቻይንኛን ለመማር ያስችልዎታል። መፅሐፉን አንብቦ ለመረዳት ምንም የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ አያስፈልግዎትም። ቻይንኛን በቀላሉ አሁኑኑ ይማሩ!

በድምፅ ቅጂ የታገዘ ትምህርት

ቋንቋን መፅሐፍ በማንበብ ብቻ መማር አይቻልም። ለዚህም ነው ይህ መፅሐፍ ከድምፅ ቅጂ ጋር ሆኖ የሚመጣው። የድምፅ ቅጂው እያንዳንዱ ቃል እንዴት እንደሚነበብ ያሳይዎታል። የሰሙትን ደጋግመው ሲናገሩ ደግሞ ልምድ ያካብታሉ።

ቻይናውያን እንዴት እንደሚነጋገሩ ይሰማሉ

ይህ መፅሐፍ የልምምድ ምዕራፎችም አሉት። በእነዚህ መዕራፎች ውስጥ ቻይናውያን ሲነጋገሩ ይሰማሉ። ስለዚህ ከቻይናውያን ጋራ በሚነጋገሩበት ጊዜ በቀላሉ ይገባዎታል!